Ethiopian News and Opinion Forum


Re: Happy MESQEL to all Orthodox Chrstian

Postby WaliaIbex » 26 Sep 2010, 18:47


እሌኒ
ንግስት እሌኒ የአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ሚስት ስትሆን ከንጉሱ ሞት በኋላ በሌሎች ሶስት ነገስታት ዘመን ከፍተኛ የአስተዳደር ስራ ፈጽማ በ1522 ከዚህ አለም በሞት አርፋለች። የተቀበረችውም በትልቅ ጥበብ ባሰራችው ቤ/ክርስቲን መርጡለ ማርያም፣ ጎጃም ነው።
እሌኒ የሃድያው ንጉስ መሐመድ ልጅ ስትሆን ዘርዓ ያዕቅብን ባገባች ጊዜ ክርስቲያን ሆናልች። አንዳንድ ታሪክ ጸሃፊያን (ለምሳሌ ባላዛር ቴሌዝ ፖርቱጋላዊው) ልጅ እንዳልነበራት ሲዘግቡ ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ ግን በልብነ ድንግል ዘመን አንዱ ወንድ ልጇ ከአምባ ግሸን አምልጦ እንደነበር መዝግቧል [1] ።
አጼ ዘርዓ ያዕቆብን የተካው ልጁ ቀዳማዊ አጼ ባእደ ማርያም እናቱ ጺዮን ሞገሴ በሞተች ግዜ እንጀራ እናቱን እሌኒን እናት ንግስት ብሎ ሾማት። ማዕረጓን በሚያስከብር ሁኔት እኩል ከንጉሱ ዘንድ አገሪቷን እንዳስተዳደረች የታሪክ ተመራማሪወች ይጽፋሉ [2]። አጼ እስክንድር ባዕደማሪያምን ሲተካ እናት ንግስቲቱ ከቤተመንግስቱ እንድትገለል ራስአምደ ሚካኤል አድርጎ ነበር። በዚህ ምክንያት በ1486 ይህ ንጉስ ከስልጣን እንዲወርድ በተደረገው ሴራ ከተካፈለች በኋላ በማንኛውም የቤተመንግስት አስተዳደር ስርዓት ውስጥ እስከ እለተ ሞቷ ተካፍይ ሆናልቸ። በአጼ ናኦድ ጊዜም ከፍተኛ ተሰሚነት ነበራት።
ናኦድ ጦርነት ላይ ሲሞት ልብነ ድንግልን እሷ እና አቡነ ማርቆስ 8ኛ ንጉስ እንዳረጉት አልቫሬዝ መዝግቧል"[3] ። የፖርቹጋሉን ፔሮ ዳ ካቭላ ምክር በመስማት በዘመኑ እያየለ የሄደውን የኦቶማን ቱርኮች ሃይል ግምት ውስጥ በማስገባት ፖርቹጋሎች ለልብነ ድንግል እርዳታ እንዲያረጉ በምቲወስ በኩል መልዕክት የላከች ይችው ንግስት ነበረች [4] ። የልብነ ድንግል ዋና ሞግዚት ሆና ከእናቱ ናኦድ ሞገሴና ከወጣቱ ንጉስ ዘመድ የጎጃሙ ራስ ደሳለኝ በመሆን ልብነ ድንግል እድሜው እስኪ ጎለምስ አገሪቱን አስተዳድራለች።
በጎጃም ክፍል ሃገርም በጣም ሰፊ የሆነ ርስት እንደነበራት አልቫሬዝ ይዘግባል.[5] ።
አልቫሬዝ የሞተች ጊዜ የሆነውን ጉዳይ እንዲህ ሲል ዘግቧል፦
የንግስት እሌኒ መሞት ወሬ በሰፊው ይሰራጭ ነበር። ሰውም "እሷ ሳለች ሁላችንም መከታ እና ከለላ አግኝተን እንኖር ንበር ፣ እሷ ስትሞት ግን ትንሽ ትልቅ ሳንል ሁላችንም ሞተናል" ይላል።
በማለት ዘግቧል። በርግጥም እሌኒ ከሞተች ከ7አመት በኋላ የግራኝ ጦርነት ተነስቶ በሁዋላ እሱዋ በጠየቀችው የፖርቹጋሎች እርዳታ አገሪቱን መከላከል ተሽሏል።

[ለማስተካከል]ዋቢ ጽሁፎች

↑ Francisco Alvarez, Prester John, p. 245
↑ Paul B. Henze, Layers of Time, A History of Ethiopia (New York: Palgrave, 2000), p. 75
↑ Alvarez, Prester John, p. 243
↑ Beckingham and Huntingford, translators, Prester John, p.307; paraphrasing the account of Gaspar Correa. Apparently Alvarez never learned this, for in his narrative he repeats without explanation Lebna Dengel's claim that Mattheus lacked the authority to represent him (e.g., p. 283).
↑ Alvarez, Prester John, pp. 425, 458.
መደብ: የኢትዮጵያ ታሪክ



Re: Happy MESQEL to all Orthodox Chrstian

Postby WaliaIbex » 26 Sep 2010, 18:50


ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም
ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ቤ/ክርስቲያን
ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም በአሁኑ ወሎ ክፍለ ሃገር፣ አምባሰል ወረዳ ውስጥ ግሸን ተራራ አናት ላይ የምትገኝ ቤ/ክርስቲያን ናት። ለዚች ቤ/ክርስቲያን መግቢያ አንድ መንገድ ብቻ ነው። እንደ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ይች ቤተ ክርስቲያን በየዘመኑ የተለያየ ስያሜን አግኝታለች።
ከአጼ ድልናአድ ዘመን (866 ዓ.ም) እስከ 11ኛው ክፍለ ዘመን በአሁኑ ስያሜ (ደብረ ከርቤ) ትታወቅ ነበር።
በ11ኛው ክፍለ ዘመን አጼ ላሊበላ ከቋጥኝ ድንጋይ ፈልፍለው እግዚአብሔር አብ የተሰኘ ቤ/ክርስቲያን በዚሁ ቦታ ሲያሰሩ ደብረ እግዜአብሔር በሚል ስም ታወቅፕች። ብዙ ሳይቆይ ግን ደብረ ነገስት ተባለች።
በ1446 አጼ ዘርአ ያዕቆብ ግማደ መስቀሉን በዚህ ስፍራ ሲያርፍ ደብረ ነገስት መባሏ ቀርቶ ደብረ ከርቤ ተባለች። በዚህ ጊዜ የነበረው የቤ/ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ መምህረ እስራኤል ዘ ደብረ ከርቤ ይባል ነበር።
አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ግማደ መስቀሉን ይዘው እየገሰገስገሱ ስለመጡ በግዕዙ "ገሰ" ወይም በአማርኛው "ገሰገሰ" የሚለው ቃል ለቦታው ስያሜ ሆነ። በዘመናት ሂደት ገስ ወደ ግሸን የሚለው ስያሜ ተዛወረ። አካባቢው በዚህ ስም ታወቀ።
የደብሩ መመስረትና የመስቀል በዓል

እንደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ትውፊት፣ የግሸንን ደብር የመሰረታት አንድ ጻድቅ መነኩሴ ነበር። ይኽውም በ514 ዓ.ም፣ ከዘርዓ ያዕቆብ መነሳት 900 አመት በፊት ነበር። የሆኖ ሆኖ አካባቢው በአሁኑ ዘመን የሚታውቀው የኢየሱስ ክርስቶስን ግማደ መስቀል በማኖሩ ነው። አጼ ዘርአ ያዕቆብ በነገሱ ዘመን ወደ ስናር ሄደው ግማደ መስቀሉንና ሌሎች ብዙ የቤ/ክርስቲያን ውድ ንዋያትን አምጥተው መስከርም 21፣ 1446 ዓ.ም ወደ ደብሩ በመውጣት በዘመኑ የነበሩትን አብያተ ክርስቲያናት እንደገና በማነጽ፤ በኋላም በእግዚአብሔር አብ ቤ/ክርስቲያን ጥግ በጥንቃቄ ጉድጓድ አስቆፍረው መስቀሉን በማስቀበርና ባለቤታቸው ንግስት እሌኒ ደብረ ከርቤ ማርያም ቤ/ክርስቲያንን እንደገና በማሳነጽ ከፍተኛ ስራ አከናወኑ። ከ5 አመት በኋላ መስከርም 21፣ 1449 ጀምሮ የመስቀል በዓል በዚህ ዕለት መከበር ተጀመረ።
Image
ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ የሚያሻግረው ብቸኛው መንገድ



Re: Happy MESQEL to all Orthodox Chrstian

Postby YEBANDAMERZE » 26 Sep 2010, 19:50


Happy Mesqel to all Ethiopians and Eritreans. Shabos don't get near a cross for it will burn your cursed body.



Re: Happy MESQEL to all Orthodox Chrstian

Postby Semira » 26 Sep 2010, 23:24


W'qaw

Lutherans are better than the recent pente arriver. They are not into brainwashing poor people like pentes do. as you said, they have a good respect to existing christianity both Orthodox and catholicism. But the Pente is not a good one. it bankrupts people mind and make them useless. the system is also against existing local traditions and wants to replace it with western styles. for instance, their females go to the pente church as if they are going to a date or night club. this is western style, but seen by this poor people as civilization.



Re: Happy MESQEL to all Orthodox Chrstian

Postby W'qaw » 27 Sep 2010, 00:09


Semira wrote:W'qaw

Lutherans are better than the recent pente arriver. They are not into brainwashing poor people like pentes do. as you said, they have a good respect to existing christianity both Orthodox and catholicism. But the Pente is not a good one. it bankrupts people mind and make them useless. the system is also against existing local traditions and wants to replace it with western styles. for instance, their females go to the pente church as if they are going to a date or night club. this is western style, but seen by this poor people as civilization.


Here is a proof!




Re: Happy MESQEL to all Orthodox Chrstian

Postby Obamajr. » 27 Sep 2010, 08:13


እንኳን ለመስቀሉ በአል አደረሳችሁ

Previous Page


Return to News & Opinion

Who is online

Registered users: Bing [Bot], Dejach Aklilu, elias, Exabot [Bot], Google [Bot], Google Adsense [Bot], Google Feedfetcher, Halafi Mengedi, Halyeyga, Macaanto, Majestic-12 [Bot], New Guy, Tit for Tat