Skip to content

Author: EthiopianReview.com

የቅንጅት ምክትል ፕሬዚደንት ብርቱካን ሚደቅሳ መኪና ተሸለሙ

በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ፈረንሳይ ለጋሲዮን እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች የአካባቢያቸው ልጅ ለሆነችው ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ መኪና በመሸለም ደስታቸውን ገለጹ፡፡ በተጨማሪም ከእስር ለተፈቱት የቅንጅት አመራሮች የምሳ ግብዣ አደረጉ፡፡ በግብዣው ላይ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም እና ወ/ት ብርቱካን ንግግር አድርገዋል፡፡ ከቀኑ አምስት ሰአት ጀምሮ ነበር ግብዣውን ያዘጋጁት የአካባቢው ነዋሪዎች ጉድ ጉድ ማለት የጀመሩት፡፡ እንግዶቹ በተጠሩበት 7፡00 ሰአት ሲመጡ ግን አካባቢው በጩኅት ተናወጠ፡፡ ሁሉም ደስታውን በጭብጨባ መግለጽ ጀመረ፡፡

ዝግጅቱ ወደተደረገበት የቀበሌ እድር አዳራሽ ሲገባ አዳራሹ ውስጥ የተሰበሰበው ህዝብ ደስታውን የሚገልጽበት ስሜት ምናልባትም ከምርጫው በሓላ የመጀመሪያው የህዝብ ስሜት ሊባል የሚችል ነበር፡፡ ሁሉም ታዳሚ የቅንጅት አርማ የሆነውን የጣት ምልክት በማውጣት በፉጨት ደስታውን ይገልጻል፡፡
አዘጋጆቹ ንግግር ካደረጉ በሓላ የምሳው ግብዣ ሥነስርአት የተከናወነ ሲሆን ኣቶ ኃይሉ ሻውል ባለመገኘታቸው የተዘጋጀላቸውን ስጦታ በልጃቸው አማካኝነት ተሰተቸዋል፡፡

በተጨማሪም ለፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም ስጦታ የተሰጠ ሲሆን ይህ ለሁለቱም የተሰጠው ስጦታ የቅንጅት አርማ የሆነው የጣት ምልክት የተቀረጸበት ዱላ ሲሆን ‹‹በትረ መንግስት›› ሲሉም ሰይመውላቸዋል፡፡

ለአቶ ሙሉነህ ኢዩኤል እና አቶ አለማየሁ ለተባለ የአካባቢቸው ወጣት ተጨማሪ ሥጦታን ከሰጡ በኋላ ለወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ሽልማት እንዳላቸው ተናገሩ፡፡ ህዝቡ ሽልማቱን ለማወቅ በከፍተኛ ጉጉት የጠበቀ ሲሆን ‹‹ጀግና›› ላለት የአካባቢያቸው ልጅ የመኪና ቁልፍ አስረከቡ፡፡ ህዝቡ ደስታውን በጭብጨባ ገለጸ፡፡

ወ/ት ብርቱካን ምን እንደምትናገር የጠፋት በሚመስል ስሜት በሁለት እጆችዋ አርማውን እያሳየች ከወገቧ በመጎንበስ ምስጋናዋን ገልጻለች፡፡ ወደ መኪናዋም በመሄድ የተሸፈነችበትን ጨርቅ ገልጣ ተረክባለች፡፡

አዘጋጆቹም ሽልማታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ‹‹አቅማችን ፈቅዶ ሁላችሁንም ብንሸልም ደሰ ባለን ነበር… ግን ለሁላችሁም የሚሆን አንድ ስጦታ አለን እሱም ልባችን ነው›› ብለዋል፡፡

ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳና ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም ረዘም ያለ ንግግር አድርገው ፕሮግራሙ ተፈጽሟል፡፡

Indian company eyes Ethiopia to grow tea

Commodity Online

In a giant move, the Kanan Devan Hills Plantations (KDHP) company of India has decided to invest Rs 375 crore in Ethiopia to develop 10,000 hectares of tea plantation.

KDHP officials said while the new project would have a 70:30 debt equity ratio, some foreign private equity companies have shown interest to participate in the venture.

The participation of Tata Tea, which already holds 20 per cent equity in KDHP, would also be sought.

The debt component would be raised from Ethiopian banks which have shown interest in the project.

The project was initiated after Ethiopian ambassador visited the tea plantations of KDHP in Munnar, which are among the largest participatory management projects in the world, and asked company officials to explore the possibilities of setting up a similar project in Ethiopia, a traditional coffee country.

A team from KDHP surveyed several potential sites before identifying 10,000 hectares of land in the South Western Oromiya district of Ethiopia for the project.

The aerial survey of the land had been completed and reached KDHP just couple of days back, along with queries on the employment and economic generation potential of the project.

According to KDHP officials, the project would create direct employment for close to 10,000 people and accelerate export and economic development of the region.

The land, which is given on 90-year lease, will command a very nominal rent.

With the nominal rent and low cost of labour, the project should be able to produce 25 million kg of high quality CTC and orthodox teas in 10 years.

Since the country has no history of tea plantations, workers from India will train Ethiopian workers. The suitability of the land is testified by the proximity to Kenya and Tanzania, which are traditional tea growing countries.

The company is in the process of preparing a detailed project report.

Over 15,000 people attended Aleqa Ayalew's funeral

Ethiopian eminent scholar and theologian Aleqa Ayalew Tamiru was buried on Thursday at Tekle Haimanot Church in Addis Ababa in the presence of over 15,000 people. Read the full report below in Amharic by an Ethiopian Review correspondent in Addis Ababa:


የአለቃ አያሌው የቀብር ስነ ስርዓት በተክለ ኃይማኖት ቤ/ክርስቲያን ተከናወነ፡፡


የአቡነ ጳውሎስን ስርዓት ከእምነትነቱ ይልቅ የካድሬ ስራ የሚሰራበት ነው በማለት በተቃውሞ ሰማዕት ሆነው የኖሩት አለቃ አያሌው ሕይወት ካለፈ በኋላ ሐሙስ ነሐሴ 17 ቀን 1999 ዓ.ም በአቡነ ተክለ ኃይማኖት በተከናወነው የቀብር ስነ ስርዓታቸው ላይ ቁጥሩ ከ15 ሺህ በላይ የሚገመት ሕዝብ ቢገኝም ካህናቱና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በዝማሬ አስክሬናቸውን ሳያጅቡ ቀሩ፡፡ በተጨማሪም የድምፅ ማጉያ እንኳን ሳያወጡ የቤተ መቅደሱን በር ዘጋግተው ጠፉ፡፡

የአለቃ አያሌው የቀብር ስነ ስርዓት በደብረሊባኖስ ገዳም ይፈፀማል ተብሎ የነበረ ሲሆን አዲስ አበባ በሚገኘው ተክለ ኃይማኖት ቤ/ክርስቲያን እንደሚፈፀም ከተሰማ በኋላ ቤተሰቦቻቸው፣ ተከታዮቻቸውና ኃዘን የተሰማቸው በሙሉ በስፍራው ተገኙ፡፡

እንኳን ለአለቃ አያሌው ይቅርና አቅሙ የጎለበተ ባለኃብት ሲሞት በቤተክስቲያኑ የሚገኙ ካህናትና ወጣቶች ልብሳቸውን ለብሰው አስክሬን ሲያጅቡና ፍታት ሲፈቱ ይስተዋል የነበረ ሲሆን በእለቱ ግን የአለቃ አያሌው የቅርብ ወዳጆች የሆኑ ካህናት ብቻ በቤታቸው ፍታት አድርገውለላቸዋል፡፡

በቀብሩ ቦታ የነበሩ አንዳንድ የእምነቱ ተከታዮች እንደተናገሩት “ምድረ የቤተ ክህነት ሰራተኛ ዛሬ ካድሬነቱ ታወቀ፡፡ የአለቃ አያሌው አስክሬን መሸኘት ያለበት በዚህ መንገድ ነበር? ምንም አይደለም ለሁሉም አንድ ቀን ያስተዛዝባል” ሲሉ ተሰምተው ነበር፡፡

የአለቃ አያሌው የበኩር ልጅ ወ/ሮ ስምረት አያሌው ስለሁኔታው ሲናገሩ “አባታችን አሁን ባለው የአባ ገ/መድህን (አቡነ ጳውሎስ) አስተዳደር ስር ያሉ ካህናት ፍትኃት እንዳያደርጉልኝ በማለታቸው ከልክለናል፡፡ ይህን ያደረግነው የአባታችንን ቃለ ውግዘት ለመጠበቅ ስንል ነው፡፡ ያስተላለፈውን ቃለ ውግዘት የሚያከብሩና የሚፈፅሙ በርካታ ምዕመናን አሉ፡፡ የቀብር ስርዓቱ በነሱ ይፈፀማል፡፡” በሚል ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

የዳግሚት ደብረሊባኖስ ደብረአሚን ፃድቁ አቡነ ተ/ኃይማኖት ምክኃ ድንግል ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በበኩላቸው የደንብ ልብሳቸውን ለብሰው ካህናቱም ልብሰ ተክህኖአቸውን አድርገው አለቃ አያሌው መኖሪያ ቤት መሄዳቸውንና ቤተሰቦቻቸው ቃለውግዘታቸውን ለመጠበቅ ሲሉ ፍታት አታደርጉም ብለው እንደመለሷቸው ተናግረዋል፡፡ አንዳንዶቹም “እኛ ቃለ ውግዘታቸው ይጠበቅ ብለን እንጂ ከፓትሪያርኩ ጋር አብረን አይደለም አስክሬኑን ያላጀብነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአለቃ አያሌው ደጋፊዎች ግን በዚህ አይስማሙም፡፡ ምንም እንኳን ቤተሰብ ቃለውግዘታቸውን ለመጠበቅ ቢከለክል ካህናቱም ሆነ ወጣቶች ልብሳቸውን እንደለሰቡ የቀብር ስርዓቱ ላይ መገኘት ይችሉ እንደነበር፤ እነሱ ግን ከዚህ ይልቅ ቤተ መቅደሱን ጠርቅመው መሄዳቸው ከኃይማኖት አስተማሪነታቸው ካድሬነታቸው እንደሚብስ ነው ያሳዩት ብለዋል፡፡

በቀብር ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት እንደታዘቡት ቤተ መቅደሱ ተጠርቅሞ ተዘግቷል፡፡ ለአለቃ አያሌው ቅኔ የሚቀኙ ወዳጆቻቸው የድምፅ ማጉያ አጥተው በቀበሌ ስብሰባ መጥሪያ ማይክራፎን ሲቀኙ ተስተውሏል፡፡

በዕለቱ በርካቶች በለቅሶ ኃዘናቸውን ይገልፃሉ፡፡ ከቤተክርስቲያኑ አናት በሚገኘው ጉልሏት አጠገብ ባለው መስታወት አንድ ሰው መጋረጃውን ገልጦ ወደህዝቡ ሲመለከት ታየ፡፡

ማን ይሆን? በሚል ይህን የተመለከትን ስንነጋገር የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ እንደሆኑ የተገመቱ ሰው መሆናቸው ታወቀ፡፡ በኋላም በተደረገው ማጣራት ካህናቱ ህሊናቸው እያወቀ የአለቃ አያሌው የቀብር ስርዓት ከውጭ እየተፈፀመ እነሱ ከውስጥ ሆነው የቤተመቅደሱን በር ጠርቅመው ቁጭ ብለዋል፡፡

ሊቀ ኅሩያን በላይ መኮንን በርካታ ቅኔ ለአለቃ አያሌው የተቀኙላቸው ሲሆን ከቅኔው መካከልም

የሦስት ሺህ ዓመት ታሪክሽን
እንደ ጁሊያን ቆጥሮ
በባህር ሀሳብ አትቶ በአቡሻ ክር ተምሮ
ታሪክ ከታሪክ አጣቅሶ
መፅሐፍ አመሳክሮ
ሳያስረዳን ወግ ባህልሽን አበጥሮ
ጥንተ ታሪክሽን አንጠርጥሮ
የተላቁ ሊቅ ያ አንደበቱ ታስሮ
በአምዓትሽ ዋዜማ
በሚሌኒየም ከተማ
አራት አይናውን አያሌውን ካጣነውማ
ምኑን ባተልን እማማ?

ሲሉ ተቀኝተውላቸዋል፡፡

በመጨረሻም ለወ/ሮ ስምረት በተሰጣቸው እድል “አለቃ አያሌው የተበላሸውን የቤተክህነት ስርዓት እየታገሉ ያለምንም ደም ሰማዕት እየከፈሉ እዚህ አድርሰዋል፡፡ አሁንም ይሄን ተጋድሎ የሚመራና ለውጤት የሚያበቃ እንዲሰጠን እግዚአብሔር ልንለምነው ይገባል” ብለዋል፡፡

በአለቃ አያሌው ቀብር የእሳቸው ዘመድና ጓደኛ ከሆኑ አንድ ካህን በስተቀር አንድም የጠቅላይ ቤተክህነት መንበረ ፓትሪያርክ ሰራተኛ አለመገኘቱን ለመታዘብ ችለናል፡፡

ለሚሌኒየሙ በመስቀል አደባባይ የሚደረጉ ዝግጅቶች ተሰረዙ

አመቱን ሙሉ ሲዘፈንለትና ሲነገርለት በነበረው የኢትዮጵያውያን ሚሌኒየም በዓል ላይ ቢያንስ ሕዝብን ሊያሳትፉ ይችላሉ ተብለው የታሰቡት የመስቀል አደባባይ ዝግጅቶች ከፀጥታ ጋር በተያያዘ ችግር ሊፈጠር ይችላል በሚል የስጋት ሰበብ ተሰረዘ፡፡ የበዓሉን ዝግጅት ያዘጋጃል በሚል ተቋቁሞ የነበረው የሚሌኒየም በዓል አከባበር ምክር ቤትም በመጨረሻ ከአንድ የዋዜማ ዝግጅት በስተቀር ሌላውን አመቱን ሙሉ ነው የምሰራው ሲል አስታውቋል፡፡

ከአቶ መለስ አንደበት ከ500 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ከውጭ ወደ አገር ውስጥ ይገባሉ ተብሎ መነገሩ በነዋሪዎቹ ላይ የኑሮ ውድነት ከመጫኑ ውጪ ምንም የታየ በርካታ እንግዳ የለም፡፡

በመስቀል አደባባይ ለስምንት ቀናት መንደር በመገንባት ዝግጅት ለማዘጋጀት ከአዲስ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤት ፍቃድ አግኝቶ የነበረው “ቴስት ኦፍ አዲስ” የተባለ ድርጅት ዝግጅቱን ማድረግ እንደማይችል በደብዳቤ ተገልፆለታል፡፡

በመስቀል አደባባይ ሚሌኒየሙን በማስመልከት ምንም አይነት ዝግጅት እንደማይደረግ በመንግስት በኩል የተገለፀ ሲሆን እንደምክንያት የተጠቀሰውም የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያውያን ሚሌኒየም በዓል እንዲደናቀፍ በየቀኑ ከሽብርተኞች ጋር መልዕክት እየተለዋወጠ በመሆኑ ለደህንነት ሲባል ክፍት በሆኑ ቦታዎች ዝግጅት አይደረግም የሚል ነው፡፡

ሚሌኒምን በሚመለከት ካሁን በኋላ በኢትዮጵያ የሚደረጉ ዝግጅቶችም በዋዜማው በስታዲየም እና በጃን ሜዳ “ሕብር” በሚል የብሔር ብሔረሰቦች ጭፈራና ቀልድ ይታያል አዘጋጁም ብሔራዊ ሚሌኒየም ጽ/ቤት ከአዲስ አበባው ጋር በመተባበር በአርቲስቶች ተሳታፊነት ነው፡፡

በተጨማሪም በቦሌ በእነ አላሙዲን በተገነባ አዳራሽ የሙዚቃ ፌስቲቫል የሚዘጋጅ ሲሆን እስረኞቹ ካልተፈቱ ኮንሰርት አላዘጋጅም በሚል መግለጫ የሰጠው ቴዲ አፍሮም በሚቀጥለው ሳምንት የሙዚቃ ኮንሰርት ያዘጋጃል፡፡

ሚሌኒየምን በዓል ለማክበር በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ይገባሉ በሚል በተነገረው መሰረት አከራዮች ለእንግዶች እናከራያለን በሚል ተከራይን ለማስለቀቅ በሚያደርጉት ጥረትና ተከራይ ከምለቅ ኪራይ እጨምራለሁ በሚል ግብ ግብ የቤት ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ከመጨመሩ ውጪ ከሆቴል ተርፎ ቤት የሚከራይ እንግዳ መምጣቱን የተመለከተ አንድም ሰው የለ፡፡

በተጨማሪም የተለያዩ ምክንያቶች የሚሰጠው የኑሮ ውድነት ከሚሌኒየሙ በዓል ጋር ሊሆን እንደሚችል በሚገመቱ አንዳንድ ምክንያቶች ለምግብነት የሚያገለግሉ እቃዎች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ውድነት ታይቷል፡፡

ከዚህ በላይ ግን ከሰኔ ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ ይጎርፋል ተብሎ የተጠበቀው ትውልደ ኢትዮጵያዊ አልፎ አልፎ በአሉን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማክበር ከሚመጡት በስተቀር እንደታሰበው እየመጣ ያለ እንግዳ የለም፡፡

የአለቃ አያሌው አስክሬን በካህናት ሳይታጀብ ቀረ

የአቡነ ጳውሎስን ስርዓት ከእምነትነቱ ይልቅ የካድሬ ስራ የሚሰራበት ነው፤ በማለት በተቃውሞ ሰማዕት ሆነው የኖሩት አለቃ አያሌው ሕይወት ካለፈ በኋላ ሐሙስ ነሐሴ 17 ቀን 1999 ዓ.ም በአቡነ ተክለ ኃይማኖት በተከናወነው የቀብር ስነ ስርዓታቸው ላይ ቁጥሩ ከ15 ሺህ በላይ የሚገመት ሕዝብ ቢገኝም ካህናቱና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በዝማሬ አስክሬናቸውን ሳያጅቡ ቀሩ፡፡ በተጨማሪም የድምፅ ማጉያ እንኳን ሳያወጡ የቤተ መቅደሱን በር ዘጋግተው ጠፉ፡፡

የአለቃ አያሌ የቀብር ስነ ስርዓት በደብረሊባኖስ ገዳም ይፈፀማል ተብሎ የነበረ ሲሆን አዲስ አበባ በሚገኘው ተክለ ኃይማኖት ቤ/ክርስቲያን እንደሚፈፀም ከተሰማ በኋላ ቤተሰቦቻቸው፣ ተከታዮቻቸውና ኃዘን የተሰማቸው በሙሉ በስፍራው ተገኙ፡፡

እንኳን ለአለቃ አያሌው ይቅርና አቅሙ የጎለበተ ባለኃብት ሲሞት በቤተክስቲያኑ የሚገኙ ካህናትና ወጣቶች ልብሳቸውን ለብሰው አስክሬን ሲያጅቡና ፍታት ሲፈቱ ይስተዋል የነበረ ሲሆን በእለቱ ግን የአለቃ አያሌው የቅርብ ወዳጆች የሆኑ ካህናት ብቻ በቤታቸው ፍታት አድርገውለላቸዋል፡፡

በቀብሩ ቦታ የነበሩ አንዳንድ የእምነቱ ተከታዮች እንደተናገሩት “ምድረ የቤተ ክህነት ሰራተኛ ዛሬ ካድሬነቱ ታወቀ የአለቃ አያሌው አስክሬን መሸኘት ያለበት በዚህ መንገድ ነበር? ምንም አይደለም ለሁሉም አንድ ቀን ያስተዛዝባል” ሲሉ ተሰምተው ነበር፡፡

የአለቃ አያሌው የበኩር ልጅ ወ/ሮ ስምረት አያሌው ስለሁኔታው ሲናገሩ “አባታችን አሁን ባለው የአቡነ ጳውሎስ አስተዳደር ስር ያሉ ካህናት ፍትኃት እንዳያደርጉልኝ በማለታቸው ከልክለናል፡፡ ይህን ያደረግነው የአባታችንን ቃለ ውግዘት ለመጠበቅ ስንል ነው፡፡ ያስተላለፈውን ቃለ ውግዘት የሚያከብሩና የሚፈፅሙ በርካታ ምዕመናን አሉ የቀብር ስርዓቱ በነሱ ይፈፀማል፡፡” በሚል ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

የዳግሚት ደብረሊባኖስ ደብረአሚን ፃድቁ አቡነ ተ/ኃይማኖት ምክኃ ድንግል ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በበኩላቸው፤ የደንብ ልብሳቸውን ለብሰው ካህናቱም ልብሰ ተክህኖአቸውን አድርገው አለቃ አያሌው መኖሪያ ቤት መሄዳቸወንና ቤተሰቦቻቸው ቃለውግዘታቸውን ለመጠበቅ ሲሉ ፍታት አታደርጉም ብለው እንደመለሷቸው ተናግረዋል፡፡ አንዳንዶቹም “እኛ ቃለ ውግዘታቸው ይጠበቅ ብለን እንጂ ከፓትሪያርኩ ጋር አብረን አይደለም አስክሬኑን ያላጀብነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአለቃ አያሌ ደጋፊዎች ግን በዚህ አይስማሙም ምንም እንኳን ቤተሰብ ቃለውግዘታቸውን ለመጠበቅ ቢከለክል ካህናቱም ሆነ ወጣቶች ልብሳቸውን እንደለሰቡ የቀብር ስርዓቱ ላይ መገኘት ይችሉ እንደነበር፤ እነሱ ግን ከዚህ ይልቅ ቤተ መቅደሱን ጠርቅመው መሄዳቸው ከኃይማኖት አስተማሪነታቸው ካድሬነታቸው እንደሚብስ ነው ያሳዩት ብለዋል፡፡

በቀብር ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት እንደታዘቡት፤ ቤተ መቅደሱ ተጠርቅሞ ተዘግቷል፡፡ ለአለቃ አያሌው ቅኔ የሚቀኙ ወዳጆቻቸው የድምፅ ማጉያ አጥተው በቀበሌ ስብሰባ መጥሪያ ማይክራፎን ሲቀኙ ተስተውሏል፡፡

በዕለቱ በርካቶች በለቅሶ ኃዘናቸውን ይገልፃሉ ከቤተክርስቲያኑ አናት በሚገኘው ጉልሏት አጠገብ ባለው መስታወት አንድ ሰው መጋረጃውን ገልጦ ወደህዝቡ ሲመለከት ታየ፡፡

ማን ይሆን? በሚል ይህን የተመለከትን ስንነጋገር የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ እንደሆኑ የተገመቱ ሰው መሆናቸው ታወቀ፡፡ በኋላም በተደረገው ማጣራት ካህናቱ ህሊናቸው እያወቀ የአለቃ አያሌው የቀብር ስርዓት ከውጭ እየተፈፀመ እነሱ ከውስጥ ሆነው የቤተመቅደሱን በር ጠርቅመው ቁጭ ብለዋል፡፡
ሊቀ ኅሩያን በላይ መኮንን በርካታ ቅኔ ለአለቃ አያሌው የተቀኙላቸው ሲሆን ከቅኔው መካከልም
የሦስት ሺህ ዓመት ታሪክሽን
እንደ ጁሊያን ቆጥሮ
በባህር ሀሳብ አትቶ በአቡሻ ክር ተምሮ
ታሪክ ከታሪክ አጣቅሶ
መፅሐፍ አመሳክሮ
ሳያስረዳን ወግ ባህልሽን አበጥሮ
ጥንተ ታሪክሽን አንጠርጥሮ
የተላቁ ሊቅ ያ አንደበቱ ታስሮ
በአምዓትሽ ዋዜማ
በሚሌኒየም ከተማ
አራት አይናውን አያሌውን ካጣነውማ
ምኑን ባተልን እማማ? ሲሉ ተቀኝተውላቸዋል፡፡

በመጨረሻም ለወ/ሮ ስምረት በተሰጣቸው እድል “አለቃ አያሌው የተበላሸውን የቤተክህነት ስርዓት እየታገሉ ያለምንም ደም ሰማዕት እየከፈሉ እዚህ አድርሰዋል፡፡ አሁንም ይሄን ተጋድሎ የሚመራና ለውጤት የሚያበቃ እንዲሰጠን እግዚአብሔር ልንለምነው ይገባል” ብለዋል፡፡

በአለቃ አያሌው ቀብር የእሳቸው ዘመድና ጓደኛ ከሆኑ አንድ ካህን በስተቀር አንድም የጠቅላይ ቤተክህነት መንበረ ፓትሪያርክ ሰራተኛ አለመገኘቱን ለመታዘብ ችለናል፡፡